ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 106:38-48 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

38. የወንዶችና የሴቶች ልጆቻቸውን ደም፣ለከነዓን ጣዖታት የሠዉአቸውን፣ንጹሕ ደም አፈሰሱ፤ምድሪቱም በደም ተበከለች።

39. በተግባራቸው ረከሱ፤በድርጊታቸውም አመንዝሮች ሆኑ።

40. ስለዚህ የእግዚአብሔር ቍጣ በሕዝቡ ላይ ነደደ፤ርስቱንም ተጸየፈ።

41. ለአሕዛብ አሳልፎ ሰጣቸው፤ጠላቶቻቸውም በላያቸው ሠለጠኑ።

42. ጠላቶቻቸው ጨቈኗቸው፤በሥልጣናቸውም ሥር አዋሏቸው።

43. እርሱ ብዙ ጊዜ ታደጋቸው፤እነርሱ ግን ዐመፃን የሙጥኝ አሉ፤በኀጢአታቸውም ተዋረዱ።

44. ሆኖም ጩኸታቸውን በሰማ ጊዜ፣ጭንቀታቸውን ተመለከተ፤

45. ለእነርሱም ሲል ቃል ኪዳኑን አሰበ፤እንደ ምሕረቱም ብዛት ከቍጣው ተመለሰ።

46. የማረኳቸው ሁሉ፣እንዲራሩላቸው አደረገ።

47. አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ፤ አድነን፤ለቅዱስ ስምህ ምስጋና እናቀርብ ዘንድ፣አንተን በመወደስ እንጓደድ ዘንድ፣ከሕዝቦች መካከል ሰብስበህ አምጣን።

48. የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር፣ከዘላለም እስከ ዘላለም ይባረክ፤ሕዝብም ሁሉ፣ “አሜን!” ይበል።ሃሌ ሉያ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 106