ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 104:5-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. ለዘላለም እንዳትናወጥ፣ምድርን በመሠረቷ ላይ አጸናሃት።

6. በጥልቁ እንደ ልብስ ሸፈንሃት፤ውሆችም ከተራሮች በላይ ቆሙ።

7. በገሠጽሃቸው ጊዜ ግን ፈጥነው ሄዱ፤የነጐድጓድህንም ድምፅ በሰሙ ጊዜ ሸሹ።

8. በተራሮች ላይ ፈሰሱ፤ወዳዘጋጀህላቸው ስፍራ፣ወደ ሸለቆዎች ወረዱ።

9. ተመልሰው ምድርን እንዳይሸፍኑ፣አልፈውም እንዳይመጡ ድንበር አበጀህላቸው።

10. ምንጮችን በሸለቆ ውስጥ እንዲሄዱ አደረግህ፤በተራሮችም መካከል ይፈሳሉ፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 104