ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 101:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ስለ ምሕረትና ስለ ፍትሕ እዘምራለሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ለአንተ በምስጋና እቀኛለሁ።

2. እንከን የማይገኝባትን መንገድ አጥብቄ እይዛለሁ፤አንተ ወደ እኔ የምትመጣው መቼ ነው?በቤቴ ውስጥ፣በንጹሕ ልብ እመላለሳለሁ።

3. በዐይኔ ፊት፣ክፉ ነገር አላኖርም።የከሓዲዎችን ሥራ እጠላለሁ፤ከእኔም ጋር አይጣበቅም።

4. ጠማማ ልብ ከእኔ ይርቃል፤ለክፋትም ዕውቅና አልሰጥም።

5. ባልንጀራውን በስውር የሚያማውን፣አጠፋዋለሁ፤ትዕቢተኛ ዐይንና ኵራተኛ ልብ ያለውን፣እርሱን አልታገሠውም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 101