ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 10:9-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. በደኑ ውስጥ እንዳለ አንበሳ በስውር ያደባል፤ረዳት የሌለውን ለመያዝ ያሸምቃል፤ድኻውንም አፈፍ አድርጎ በወጥመዱ ይጐትታል።

10. ምስኪኑም ይደቃል፤ ዐንገቱን ይደፋል፤ያልታደለውም በክንዱ ሥር ይወድቃል።

11. በልቡም፣ “እግዚአብሔር ረስቶአል፤ፊቱን ሸፍኖአል፤ ፈጽሞም አያይም”ይላል።

12. እግዚአብሔር ሆይ ተነሥ፤ አምላክ ሆይ፤ ክንድህን አንሣ፤ረዳት የሌላቸውንም አትርሳ።

13. ክፉ ሰው በእግዚአብሔር ላይ ለምን ክፉ ይናገራል?በልቡስ፣ “ስለ ሥራዬ አይጠይቀኝም”ለምን ይላል?

14. አንተ ግን መከራንና ሐዘንን ታያለህ፤በእጅህም ዋጋ ለመክፈል ትመለከታለህ፤ምስኪኑም ራሱን በአንተ ላይ ይጥላል፤ለድኻ ዐደግም ረዳቱ አንተ ነህ።

15. የክፉውንና የበደለኛውን ክንድ ስበር፤የእጁንም ስጠው፤ምንም እስከማይገኝ ድረስ።

16. እግዚአብሔር ከዘላለም እስከ ዘላለም ንጉሥ ነው፤ሕዝቦችም ከምድሩ ይጠፋሉ።

17. እግዚአብሔር ሆይ፤ የተገፉትን ምኞት ትሰማለህ፤ልባቸውን ታበረታለህ፤ ጆሮህንም ወደ እነርሱ ጣል ታደርጋለህ፤

18. ከዐፈር የተፈጠረ ሰው ከእንግዲህእንዳያስጨንቃቸው፣አንተ ለድኻ ዐደጉና ለተገፋው ትሟገታለህ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 10