ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መክብብ 9:13-17 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. እንዲሁም እጅግ ያስገረመኝን ይህን የጥበብ ምሳሌ ከፀሓይ በታች አየሁ፦

14. ጥቂት ሰዎች የሚኖሩባት አንዲት ትንሽ ከተማ ነበረች፤ አንድ ኀያል ንጉሥም መጣባት፤ ከበባት፤ በላይዋም ትልቅ ምሽግ ሠራባት።

15. በዚያችም ከተማ ጥበበኛ የሆነ አንድ ድኻ ሰው ይኖር ነበር፤ በጥበቡም ከተማዋን አዳናት፤ ነገር ግን ያን ድኻ ማንም አላስታወሰውም።

16. ስለዚህ፣ “ጥበብ ከኀይል ይበልጣል” አልሁ፤ ሆኖም የድኻው ጥበብ ተንቆአል፤ ቃሉም አልተሰማም።

17. ሞኞችን ከሚያስተዳድር ገዥ ጩኸት ይልቅ፣ጠቢብ በዝግታ የሚናገረው ቃል ይደመጣል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መክብብ 9