ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መክብብ 7:3-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. ሐዘን ከሣቅ ይሻላል፤ያዘነ ፊት ለልብ መልካም ነውና።

4. የጠቢባን ልብ በሐዘን ቤት ነው፤የሞኞች ልብ ግን በደስታ ቤት ነው።

5. የሞኞችን መዝሙር ከመስማት፣የጠቢባንን ሰዎች ተግሣጽ መስማት ይሻላል።

6. የሰነፎች ሣቅ፣ከድስት ሥር እንደሚንጣጣ የእሾኽ ማገዶ ነው፤ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።

7. ግፍ ጠቢብን ሞኝ ያደርጋል፤ጒቦም ልብን ያበላሻል።

8. የአንድ ነገር ፍጻሜ ከጅማሬው ይሻላል፤ትዕግሥተኛም ከትዕቢተኛ ይሻላል፤

9. የሞኞች ቊጣ በዕቅፋቸው ውስጥ ስለ ሆነ፣በመንፈስህ ለቊጣ አትቸኵል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መክብብ 7