ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መክብብ 7:20-28 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

20. ትክክለኛውን ነገር የሚያደርግና ፈጽሞ ኀጢአት የማይሠራ፣ጻድቅ ሰው በምድር ላይ የለም።

21. የሚነገረውን ቃል ሁሉ ለማዳመጥ አትሞክር፤አለበለዚያ አገልጋይህ ሲረግምህ ትሰማ ይሆናል፤

22. ብዙ ጊዜ አንተ ራስህ፣ሌሎችን እንደረገምህ ልብህ ያውቃልና።

23. እኔም ይህን ሁሉ በጥበብ ፈትኜ፣“ጠቢብ ለመሆን ቈርጫለሁ” አልሁ፤ይህ ግን ከእኔ የራቀ ነበር።

24. ጥበብ ምንም ይሁን ምን፣እጅግ ጥልቅና ሩቅ ነው፤ማንስ ሊደርስበት ይችላል?

25. ስለዚህ ጥበብንና የነገሮችን አሠራር ለመመርመርና ለማጥናት፣የክፋትን መጥፎነት፣የሞኝነትንም እብደት ለማስተዋል፣አእምሮዬን መለስሁ።

26. ልቧ ወጥመድ፣እጆቿም እግር ብረት የሆኑ፣አሽክላ የሆነች፣ከሞት የከፋችዋን ሴት አገኘሁ፤እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ከእጇ ያመልጣል፤ኀጢአተኛውን ግን አጥምዳ ትይዘዋለች።

27. ሰባኪው እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ መርምሬ ያገኘሁት ነገር ይህ ነው፤“የነገሮችን ብልኀት መርምሮ ለማግኘት፣አንዱን በአንዱ ላይ በመጨመር፣

28. ገና በመመርመር ላይ ሳለሁ፣ግን ያላገኘሁት፣ከሺህ ወንዶች መካከል አንድ ቅን ሰው አገኘሁ፣በእነዚያ ሁሉ መካከል ግን አንዲት ቅን ሴት አላገኘሁም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መክብብ 7