ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መክብብ 6:3-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. አንድ ሰው መቶ ልጅ ሊኖረውና ብዙ ዓመት ሊኖር ይችላል፤ ምንም ያህል ይኑር፣ በሀብቱ ደስ ካልተሰኘበትና በአግባብ ካል ተቀበረ፣ ከእርሱ ይልቅ ጭንጋፍ ይሻላል እላለሁ፤

4. ምክንያቱም በከንቱ ይመጣል፤ በጨለማም ይሄዳል፤ ስሙም በጨለማ ተሸፍኖአል።

5. ፀሓይን ባያይና ምንም ነገር ባያውቅ እንኳ፣ እርሱ ከዚያ ሰው ይልቅ ዕረፍት አለው፤

6. ሁለት ጊዜ ሺህ ዓመት ቢኖር ነገር ግን በሀብቱ ደስ ባይሰኝበት ሁሉ ወደዚያ ስፍራ የሚሄድ አይደለምን?

7. የሰው ጥረት ሁሉ ለአፉ ነው፤ፍላጎቱ ግን ፈጽሞ አይረካም።

8. ጠቢብ ከሞኝ ይልቅ ምን ብልጫ አለው?ድኻስ በሌሎች ፊት እንዴት እንደሚኖር በማወቁ፣ትርፉ ምንድን ነው?

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መክብብ 6