ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መክብብ 6:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ከፀሓይ በታች ሌላ ክፉ ነገር አየሁ፤ እርሱም ለሰዎች እጅግ የሚከብድ ነው፤

2. ሰው ልቡ የሚሻውን እንዳያጣ፣ እግዚአብሔር ባለጠግነትን፣ ሀብትንና ክብርን ይሰጠዋል፤ እግዚአብሔር ግን እንዲደሰትበት ሥልጣን አልሰጠውም፤ ይልቁን ባዕድ ይደሰትበታል። ይህም ከንቱ፣ እጅግም ክፉ ነገር ነው።

3. አንድ ሰው መቶ ልጅ ሊኖረውና ብዙ ዓመት ሊኖር ይችላል፤ ምንም ያህል ይኑር፣ በሀብቱ ደስ ካልተሰኘበትና በአግባብ ካል ተቀበረ፣ ከእርሱ ይልቅ ጭንጋፍ ይሻላል እላለሁ፤

4. ምክንያቱም በከንቱ ይመጣል፤ በጨለማም ይሄዳል፤ ስሙም በጨለማ ተሸፍኖአል።

5. ፀሓይን ባያይና ምንም ነገር ባያውቅ እንኳ፣ እርሱ ከዚያ ሰው ይልቅ ዕረፍት አለው፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መክብብ 6