ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መክብብ 4:2-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. እኔም የቀድሞ ሙታን፣ዛሬ በሕይወት ካሉት ሕያዋን ይልቅ፣ደስተኞች እንደሆኑ ተናገርሁ።

3. ነገር ግን ከሁለቱም ይልቅ፣ገና ያልተወለደው፣ከፀሓይ በታች የሚደረገውንም፣ክፋት ያላየው ይሻላል።

4. እንዲሁም ጥረትና የሥራ መከናወን ሁሉ ሰው በባልንጀራው ላይ ካለው ቅናት እንደሚመነጭ ተመለከትሁ፤ ይህም ደግሞ ከንቱ፣ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።

5. ሰነፍ እጁን አጣጥፎ ይቀመጣል፤የገዛ ራሱንም ሥጋ ይበላል።

6. በድካምና ነፋስን በመከተል ከሚገኝ ሁለት ዕፍኝ ይልቅ፣በርጋታ የሚገኝ አንድ ዕፍኝ ይሻላል።

7. ደግሞም ከፀሓይ በታች ከንቱ የሆነን ነገር አየሁ፤

8. ልጅም ሆነ ወንድም የሌለው፣ብቸኛ ሰው አለ፤ጥረቱ ማለቂያ የለውም፤ ዐይኑም ባለው ሀብት ገና አልረካም፤እርሱም፣ “ለማን ብዬ ነው የምደክመው?ራሴን ከማስደሰትስ የምቈጠበውለምንድን ነው?” ብሎ ጠየቀ፤ይህም ደግሞ ከንቱ፣ የጭንቅ ኑሮ ነው።

9. ለሥራቸው መልካም ውጤት ስለሚያገኙ፣ከአንድ፣ ሁለት መሆን ይሻላል፤

10. አንዱ ቢወድቅ፣ባልንጀራው ደግፎ ያነሣዋል።ቢወድቅ የሚያነሣው ረዳት የሌለው ግን፣እንዴት አሳዛኝ ነው!

11. ደግሞም ሁለቱ አብረው ቢተኙ ይሞቃቸዋል፤ነገር ግን አንዱ ብቻውን እንዴት ሊሞቀው ይችላል?

12. አንድ ሰው ብቸኛውን ቢያጠቃውም፣ሁለት ከሆኑ ይመክቱታል፤በሦስት የተገመደ ገመድም ቶሎ አይበጠስም።

13. ምክርን መቀበል ከማያውቅ ሞኝና ሽማግሌ ንጉሥ ይልቅ ጠቢብ የሆነ ድኻ ወጣት ይሻላል።

14. ወጣቱ ከእስር ቤት ወደ ንጉሥነት የመጣ ወይም በግዛቱ ውስጥ በድኽነት የተወለደ ሊሆን ይችላል።

15. ከፀሓይ በታች የሚኖሩና የሚመላለሱ ሁሉ፣ ንጉሡን የሚተካውን ወጣት ተከትለውት አየሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መክብብ 4