ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መክብብ 3:1-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ለሁሉም ነገር ጊዜ አለው፤ከሰማይ በታች ለሚከናወነው ለማንኛውም ነገር ወቅት አለው፤

2. ለመወለድ ጊዜ አለው፤ ለመሞትም ጊዜ አለው፤ለመትከል ጊዜ አለው፤ ለመንቀልም ጊዜ አለው፤

3. ለመግደል ጊዜ አለው፤ ለማዳንም ጊዜ አለው፤ለማፍረስ ጊዜ አለው፤ ለመገንባትም ጊዜ አለው፤

4. ለማልቀስ ጊዜ አለው፤ ለመሣቅም ጊዜ አለው፤ለሐዘን ጊዜ አለው፤ ለጭፈራም ጊዜ አለው፤

5. ድንጋይ ለመጣል ጊዜ አለው፤ ድንጋይ ለመሰብሰብም ጊዜ አለው፤ለመተቃቀፍ ጊዜ አለው፤ ለመለያየትም ጊዜ አለው፤

6. ለመፈለግ ጊዜ አለው፤ ለመተው ጊዜ አለው፤ለማስቀመጥ ጊዜ አለው፤ አውጥቶ ለመጣልም ጊዜ አለው፤

7. ለመቅደድ ጊዜ አለው፤ ለመስፋትም ጊዜ አለው፤ለዝምታ ጊዜ አለው፤ ለመናገርም ጊዜ አለው፤

8. ለመውደድ ጊዜ አለው፤ ለመጥላትም ጊዜ አለው፤ለጦርነት ጊዜ አለው፤ ለሰላምም ጊዜ አለው።

9. ሠራተኛ ከጥረቱ የሚያገኘው ትርፍ ምንድን ነው?

10. ሰዎች ይደክሙበት ዘንድ እግዚአብሔር የሰጣቸውን ከባድ የሥራ ጫና አየሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መክብብ 3