ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መክብብ 11:3-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. ደመናት ውሃ ካዘሉ፣በምድር ላይ ዝናብን ያዘንባሉ፤ዛፍ ወደ ደቡብም ሆነ ወደ ሰሜን ቢወድቅ፣በወደቀበት ቦታ በዚያ ይጋደማል።

4. ነፋስን የሚጠባበቅ አይዘራም፤ደመናትንም የሚያይ አያጭድም።

5. የነፋስን መንገድ እንደማታውቅ፣ሕይወት ወይም መንፈስ በእናት ማሕፀን ውስጥ ወደሚገኘው አካል እንዴት እንደሚገባም እንደማታውቅ ሁሉ፣ሁሉን ሠሪ የሆነውን፣ የእግዚአብሔርን ሥራማስተዋል አትችልም።

6. ጠዋት ላይ ዘርህን ዝራ፤ማታም ላይ እጅህ ሥራ አይፍታ፤ይህ ወይም ያ፣ወይም ሁለቱ መልካም ይሁኑ፣የቱ እንደሚያፈራ አታውቅምና።

7. ብርሃን መልካም ነው፤ፀሓይንም ማየት ለዐይን ደስ ያሰኛል።

8. ሰው ምንም ያህል ብዙ ዓመት ቢኖር፣በእነዚህ ሁሉ ይደሰት፤ነገር ግን ጨለማዎቹንም ቀናት ያስብ፤እነርሱ ይበዛሉና፤የሚመጣውም ነገር ሁሉ ከንቱ ነው።

9. አንተ ወጣት በወጣትነትህ ጊዜ ደስ ይበልህ፤በወጣትነትህም ዘመን ልብህ ደስ ያሰኝህ፤የልብህን መንገድ፣ዐይንህ የሚያየውንም ሁሉ ተከተል፤ነገር ግን ስለ እነዚህ ነገሮች ሁሉ፣እግዚአብሔር ወደ ፍርድ እንደሚያመጣህ ዕወቅ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መክብብ 11