ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መክብብ 10:8-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. ጒድጓድን የሚምስ ራሱ ይገባበታል፤ቅጥርንም የሚያፈርስ እባብ ይነድፈዋል።

9. ድንጋይ የሚፈነቅል ይጐዳበታል፤ግንድንም የሚፈልጥ አደጋ ላይ መውደቁ አይቀርም።

10. መጥረቢያ ቢደንዝ፣ጫፉም ባይሳል፣ብዙ ጒልበት ይጨርሳል፤ብልኀት ግን ለውጤት ያበቃል።

11. እባብ በድግምት ከመፍዘዙ በፊት ቢነድፍ፣ለደጋሚው ምንም አይጠቅመውም።

12. ከጠቢብ አፍ የሚወጣ ቃል ባለ ሞገስ ነው፤ሞኝ ግን በገዛ ከንፈሩ ይጠፋል፤

13. ቃሉ በመጀመሪያ ሞኝነት ነው፤በመጨረሻም ደግሞ ክፉ እብደት ነው፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መክብብ 10