ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መክብብ 10:4-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. የገዥ ቊጣ በተነሣብህ ጊዜ፣ስፍራህን አትልቀቅ፤ትዕግሥት ታላቁን ጥፋት ጸጥ ያደርጋልና።

5. ከፀሓይ በታች ያየሁት ክፉ ነገር አለ፤ይህም ከገዥ የሚወጣ ስሕተት ነው፤

6. ሞኞች በብዙ የክብር ስፍራዎች ሲቀመጡ፣ሀብታሞች ግን በዝቅተኛ ስፍራ ሆነዋል።

7. መሳፍንት እንደ ባሮች በእግራቸው ሲሄዱ፣ባሮች ፈረስ ላይ ተቀምጠው አይቻለሁ።

8. ጒድጓድን የሚምስ ራሱ ይገባበታል፤ቅጥርንም የሚያፈርስ እባብ ይነድፈዋል።

9. ድንጋይ የሚፈነቅል ይጐዳበታል፤ግንድንም የሚፈልጥ አደጋ ላይ መውደቁ አይቀርም።

10. መጥረቢያ ቢደንዝ፣ጫፉም ባይሳል፣ብዙ ጒልበት ይጨርሳል፤ብልኀት ግን ለውጤት ያበቃል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መክብብ 10