ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መክብብ 10:17-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

17. አንቺ ንጉሥሽ ከተከበረው ዘር የሆነ፣ለመስከር ሳይሆን ለብርታት፣በተገቢው ጊዜ የሚበሉ መሳፍንት ያሉሽ ምድር ሆይ፤ የተባረክሽ ነሽ፤

18. ሰው ሰነፍ ከሆነ ጣራው ይዘብጣል፤እጆቹም ካልሠሩ ቤቱ ያፈሳል።

19. ግብዣ ለሣቅ ያዘጋጃል፤ወይንም ሕይወትን ያስደስታል፤ገንዘብም ካለ ሁሉ ነገር አለ።

20. በሐሳብህም እንኳ ንጉሥን አትንቀፍ፤በመኝታ ክፍልህም ባለጠጋን አትርገም፤የሰማይ ወፍ ቃልህን ልትወስድ፣የምትበረዋም ወፍ የምትለውን ልታደርስ ትችላለችና።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መክብብ 10