ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መክብብ 1:1-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. በኢየሩሳሌም የነገሠው፣ የዳዊት ልጅ፣ የሰባኪው ቃል፤

2. ሰባኪው፣“ከንቱ፣ ከንቱ፣የከንቱ ከንቱ፤ሁሉም ነገር ከንቱ ነው” ይላል።

3. ከፀሓይ በታች ከሚለፋበት ተግባር ሁሉ፣ሰው ምን ትርፍ ያገኛል?

4. ትውልድ ይሄዳል፤ ትውልድ ይመጣል፤ምድር ግን ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች።

5. ፀሓይ ትወጣለች፤ ትጠልቃለችም፤ወደምትወጣበትም ለመመለስ ትጣደፋለች።

6. ነፋስ ወደ ደቡብ ይነፍሳል፤ወደ ሰሜንም ይመለሳል፤ዞሮ ዞሮ ይሄዳል፤ዘወትርም ወደ ዑደቱ ይመለሳል።

7. ወንዞች ሁሉ ወደ ባሕር ይፈሳሉ፤ባሕሩ ግን ፈጽሞ አይሞላም፤ወንዞች ወደ መጡበት ስፍራ፣ወደዚያ እንደ ገና ይመለሳሉ።

8. ሰው መናገር ከሚችለው በላይ፣ነገሮች ሁሉ አድካሚ ናቸው፤ዐይን ከማየት አይጠግብም፤ጆሮም በመስማት አይሞላም።

9. የነበረው ነገር እንደ ገና ይሆናል፤የተደረገውም ተመልሶ ይደረጋል፤ከፀሓይ በታች ምንም አዲስ ነገር የለም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መክብብ 1