ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መሳፍንት 8:31-35 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

31. በሴኬም የምትኖረው ቁባቱም እንደዚሁ ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ ስሙንም አቤሜሌክ አለው።

32. የኢዮአስ ልጅ ጌዴዎን ዕድሜ ጠግቦ ሞተ፤ በአቢዔዝራውያን ምድር ባለችው በዖፍራ፣ በአባቱ በኢዮአስ መቃብር ተቀበረ።

33. ጌዴዎን ሞቶ ብዙም ሳይቈይ እስራኤላውያን የበኣልን አማልክት በማምለክ አመነዘሩ፤ በኣልብሪትንም አምላካቸው አደረጉ፤

34. በዙሪያቸው ከነበሩት ጠላቶቻቸው እጅ የታደጋቸውን እግዚአብሔር አምላካቸውን አላሰቡትም።

35. እንዲሁም ይሩባኣል የተባለው ጌዴዎን ያደረገላቸውን በጎ ነገር ሁሉ አስበው ለቤተ ሰቡ ውለታ መላሽ ሆነው አልተገኙም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መሳፍንት 8