ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መሳፍንት 5:21-28 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

21. ጥንታዊው ወንዝ፣ የቂሶን ወንዝ፣የቂሶን ወንዝ ጠርጐ ወሰዳቸው፤ነፍሴ ሆይ፤ በኀይል ገሥግሺ

22. የፈረሶች ኮቴ ድምፅ በኀይል ተሰማ፤ጋለቡ፤ በኀይልም ፈጥነው ጋለቡ።

23. የእግዚአብሔር መልአክ፣ ‘ሜሮዝን ርገሙ፤’‘ሕዝቧንም አብራችሁ ርገሙ፤ከኀያላን ሰልፍ እግዚአብሔርን ለመርዳት፣በእግዚአብሔርም ጐን ለመቆም አልመጡምና’ አለ።

24. ‘የቄናዊው የሔቤር ሚስት ኢያዔል፣ከሴቶች ሁሉ የተባረከች ትሁን፤በድንኳን ከሚኖሩ ሴቶች ሁሉ የተባረከች ትሁን።

25. ውሃ ለመነ፤ ወተት ሰጠችው፤ለመኳንንት በሚገባ ዕቃ፣ እርጎ አቀረበችለት።

26. እጇዋ ካስማ ያዘ፤ቀኝ እጇም የሠራተኛ መዶሻ ጨበጠ፤ሲሣራን መታችው፤ ራሱንም ተረከከችው፤ክፉኛ ወጋችው፤ ጆሮ ግንዱን በሳችው።

27. በእግሯ ሥር ተደፋ፤ ወደቀ፤በዚያም ተዘረረ፤ በእግሯ ሥር ተደፋ፤ወደቀ፤ በተደፋበት በዚያ ወደቀ፤ሞተም።

28. “የሲሣራ እናት በመስኮት ተመለከተች፤በዐይነ ርግቡ ቀዳዳም ጮኻ ተጣራች፤‘ለምን ሠረገላው ሳይመጣ ዘገየ?የሠረገሎቹስ ድምፅ ለምን ጠፋ?’ አለች።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መሳፍንት 5