ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መሳፍንት 21:11-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. እነርሱም፣ “እንግዲህ የምታደርጉት ይህ ነው፤ ወንዱን በሙሉ እንዲሁም ድንግል ያልሆኑትን ሴቶች ሁሉ ግደሉ” አሏቸው።

12. በኢያቢስ ገለዓድ ከሚኖረው ሕዝብ መካከል ወንድ ያልደረ ሰባቸው አራት መቶ ደናግል አገኙ፤ በከነዓን ምድር በሴሎ ወደ ሚገኘውም ሰፈር አመጧቸው።

13. ከዚያም ጉባኤው በሙሉ በሬሞን ዐለት ወዳሉት ብንያማውያን የሰላም ጥሪ አስተላለፈ።

14. ስለዚህ በዚህን ጊዜ ብንያማውያን ተመለሱ፤ ከመገደል የተረፉትንም የኢያቢስ ገለዓድ ሴቶች ሰጧቸው፤ ይሁን እንጂ የሴቶቹ ቊጥር ለሁሉም የሚበቃ አልነበረም።

15. እግዚአብሔር በእስራኤል ነገዶች መካከል አስደንጋጭ ስብራት ስላደረገ የእግዚአብሔር ሕዝብ ለብንያማውያን አዘነ።

16. የጉባኤውም መሪዎች እንዲህ አሉ፤ “እነሆ፤ የብንያም ሴቶች አልቀዋል፤ ታዲያ ለቀሩት ወንዶች ሚስት የምናገኝላቸው እንዴት ነው?

17. ከእስራኤል ነገዶች አንዱ የሆነው እንዳይጠፋ አሁን በሕይወት ያሉት ብንያማውያን ወራሽ የሚሆን ዘር ሊኖራቸው ይገባል።

18. ‘ልጁን ለብንያማዊ የሚድር ርጉም ይሁን’ ብለን እኛ እስራኤላውያን ስለ ተማማልን እንግዲህ ልጆቻችንን ልንድርላቸው አንችልም፤

19. ይሁን እንጂ ከቤቴል በስተ ሰሜንና ከቤቴል ወደ ሴኬም በሚወስደው መንገድ በስተ ምሥራቅ እንዲሁም ከለቦና በስተ ደቡብ ባለችው በሴሎ የእግዚአብሔር በዓል በየዓመቱ ይከበራል።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መሳፍንት 21