ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መሳፍንት 15:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ከጥቂት ጊዜ በኋላ በስንዴ መከር ወራት ሳምሶን አንድ የፍየል ጠቦት ይዞ ሚስቱን ለማየት ሄደ፤ እርሱም፣ “ሚስቴ ወዳለችበት ጫጒላው ቤት ልግባ” አለ፤ አባቷ ግን እንዲገባ አልፈቀደለትም።

2. አባትየውም፣ ፈጽሞ የጠላሃት መሆንህን ስለ ተረዳሁ ለሚዜህ ድሬለታለሁ፤ ታናሽ እኅቷ ከእርሷ ይልቅ ውብ አይደለችምን? እርሷን አግባት” አለው።

3. ሳምሶንም መልሶ፣ “ከእንግዲህ በፍልስጥኤማውያን ላይ በሚደርሰው ጒዳት ተጠያቂ አልሆንም” አላቸው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መሳፍንት 15