ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መሳፍንት 10:4-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. ኢያዕር በሠላሳ አህዮች የሚጋልቡ ሠላሳ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ ልጆቹም እስከ ዛሬ ድረስ የኢያዕር መንደሮች ተብለው የሚጠሩ ሠላሳ ከተሞች በገለዓድ ምድር ነበሯቸው።

5. ኢያዕር ሞተ፤ በቃሞንም ተቀበረ።

6. እስራኤላውያን እንደ ገና በእግዚአብሔር ላይ ክፉ ድርጊት ፈጸሙ፤ በኣልንና አስታሮትን እንዲሁም የሶሪያን፣ የሲዶናን፣ የሞዓብን፣ የአሞንንና የፍልስጥኤማውያንን አማልክት አመለኩ፤ እስራኤላውያን እግዚአብሔርን ስለተዉና ስላላገለገሉት፣

7. ተቈጣቸው፤ በፍልስጥኤማውያንና በአሞናውያን እጅ ሸጣቸው፤

8. እነርሱም በዚያን ዓመት ሰበሯቸው፤ አደቀቋቸውም፤ እስራኤላውያንን ሁሉ ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ባለው በገለዓድ ምድር፣

9. በአሞራውያን አገር ዐሥራ ስምንት ዓመት እንዲሁም አሞናውያን ይሁዳን፣ ብንያምንና የኤፍሬምን ቤት ለመውጋት ዮርዳኖስን ስለ ተሻገሩ እስራኤላውያን እጅግ ተጨነቁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መሳፍንት 10