ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሕዝቅኤል 47:13-23 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ምድሪቱን ርስት አድርገህ ለዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ የምታከፋፍሉባቸው፣ ወሰኖች እነዚህ ናቸው፤ ዮሴፍ ሁለት ዕጣ ይኑረው።

14. እኩል አድርጋችሁ ከፋፍሉት፤ ለቀድሞ አባቶቻችሁ እሰጣቸው ዘንድ በተዘረጋች እጅ ስለ ማልሁ፣ ምድሪቱ ርስታችሁ ትሆናለች።

15. “የምድሪቱ ወሰን ይህ ነው፤“በሰሜን በኩል ከታላቁ ባሕር አንሥቶ በሔትሎን መንገድ በሐማት መተላለፊያ አድርጎ እስከ ጽዳድ ይደርሳል፤

16. ከዚያም ቤሮታን፣ በደማስቆና በሐማት ወሰን መካከል ያለውን ሲብራይምን ዐልፎ፣ በሐውራን ወሰን ላይ እስካለው እስከ ሐጸርሃቲኮን ይዘልቃል።

17. ወሰኑ ከባሕሩ በመነሣት፣ በሰሜኑ የደማስቆ ድንበር አድርጎ፣ የሐማትንም ዳርቻ ወደ ሰሜን ትቶ እስከ ሐጸርዔናን ይዘልቃል።

18. “በምሥራቅ በኩል ወሰኑ በሐውራንና በደማስቆ መካከል፣ በገለዓድና በእስራኤል ምድር መካከል ዮርዳኖስ ይሆናል፤ የምሥራቁ ድንበር እስከ ምሥራቁ ባሕር ይወርድና እስከ ታማር ይዘልቃል፤ ይህም የምሥራቁ ወሰን ይሆናል።

19. “በደቡብ በኩል ወሰኑ ከታማር ይነሣና እስከ ሜሪባ ቃዴስ ውሃ ይደርሳል፤ ከዚያም የግብፅን ደረቅ ወንዝ ተከትሎ እስከ ታላቁ ባሕር ይዘልቃል፤ ይህ የደቡቡ ወሰን ነው።

20. “በምዕራቡ በኩል ወሰኑ ከሐማት መግቢያ ፊት ለፊት እስካለው ቦታ ድረስ ታላቁ ባሕር ይሆናል፤ ይህም የምዕራቡ ወሰን ይሆናል።

21. “እነሆ፤ ይህችን ምድር በእስራኤል ነገድ ቍጥር ልክ ትከፋፈላላችሁ፤

22. ለራሳችሁ፣ በመካከላችሁ ለሚኖሩት ልጆች ላሏቸው መጻተኞች ርስት አድርጋችሁ መድቡ፤ እነርሱንም እንደ እስራኤል ተወላጆች ቍጠሯቸው፤ እንደ እናንተ ከእስራኤል ነገዶች ርስት ይመደብላቸው።

23. መጻተኛ በማንኛውም ነገድ መካከል ቢቀመጥ፣ በዚያ ርስቱን ስጡት” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሕዝቅኤል 47