ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሕዝቅኤል 42:8-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. ከውጩ አደባባይ ቀጥሎ ያሉት መደዳ ክፍሎች ርዝመት አምሳ ክንድ ሲሆን፣ ከቤተ መቅደሱ አጠገብ ያሉት መደዳ ክፍሎች ርዝመት ደግሞ አንድ መቶ ክንድ ነበር።

9. ከውጩ አደባባይ ወደ ውስጥ ሲገባ፣ በስተ ምሥራቅ የታችኞቹ ክፍሎች መግቢያ ይገኛል።

10. በደቡብ በኩል የውጩን አደባባይ ግንብ ተከትሎ፣ ከቤተ መቅደሱ አደባባይ ጋር የተያያዙና ከውጩ ግንብ ጋር ትይዩ የሆኑ ክፍሎች አሉ፤

11. ከፊት ለፊታቸውም መተላለፊያ መንገድ አለ። እነዚህ በሰሜን በኩል ካሉት ክፍሎች ጋር ተመሳሳይ ሲሆኑ፣ ርዝመትና ወርዳቸው፣ መውጫና መጠናቸው አንድ ዐይነት ነበር፤ በሰሜን በኩል እንዳሉት በሮች፣

12. በደቡብ በኩል ያሉት ክፍሎች በሮች መጠናቸው ተመሳሳይ ነበር። ከመመላለሻው መነሻ ላይ መግቢያ በር አለ፤ መመለሻውም ፊት ለፊት ካለው ወደ ምሥራቅ ከሚያመራው ግንብ ጋር ተጓዳኝ ነው።

13. ከዚያም እንዲህ አለኝ፤ “ከቤተ መቅደሱ አደባባይ ፊት ለፊት ያሉት የሰሜኑና የደቡቡ ክፍሎች የካህናቱ ሲሆኑ፣ እነዚህም በእግዚአብሔር ፊት የሚቀርቡት ካህናት እጅግ የተቀደሱትን ቍርባኖች የሚበሉባቸው ናቸው። በዚያም እጅግ የተቀደሱትን ቍርባኖች ማለት የእህሉን ቍርባን፣ የኀጢአቱን ቍርባን፣ የበደሉን ቍርባን ያስቀምጣሉ፤ ቦታው ቅዱስ ነውና።

14. ካህናቱ አንድ ጊዜ ወደ ተቀደሰው ቦታ ከገቡ በኋላ፣ ያገለገሉበትን ልብስ ሳያወልቁ ወደ ውጩ አደባባይ መውጣት አይችሉም፤ የተቀደሰ ነውና፤ ወደ ሕዝቡ ቦታ ከመምጣታቸው በፊት ሌላውን ልብሳቸውን መልበስ አለባቸው።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሕዝቅኤል 42