ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሕዝቅኤል 42:14-17 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. ካህናቱ አንድ ጊዜ ወደ ተቀደሰው ቦታ ከገቡ በኋላ፣ ያገለገሉበትን ልብስ ሳያወልቁ ወደ ውጩ አደባባይ መውጣት አይችሉም፤ የተቀደሰ ነውና፤ ወደ ሕዝቡ ቦታ ከመምጣታቸው በፊት ሌላውን ልብሳቸውን መልበስ አለባቸው።”

15. በቤተ መቅደሱ ውስጥ ያለውን ስፍራ ለክቶ ከጨረሰ በኋላ፣ በምሥራቅ በር በኩል ወደ ውጩ አወጣኝ፤ በዙሪያው ያለውንም ስፍራ ሁሉ ለካ፤

16. በምሥራቅ ያለውንም በመለኪያው ዘንግ ለካ፤ አምስት መቶ ክንድ ሆነ።

17. ሰሜኑንም ለካ፤ በመለኪያው ዘንግ አምስት መቶ ክንድ ሆነ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሕዝቅኤል 42