ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሕዝቅኤል 41:6-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. ግራና ቀኝ ያሉት ክፍሎች፣ ባለ ሦስት ደርብ ናቸው፤ በእያንዳንዱም ደርብ ላይ ሠላሳ ክፍሎች ነበሩ፤ በግንቡም ዙሪያ ግራና ቀኝ ያሉትን እነዚህን ክፍሎች ደግፈው የሚይዙ ተሸካሚዎች ነበሩ፤ ሆኖም ተሸካሚዎቹ ወደ ቤተ መቅደሱ ግንብ ዘልቀው አልገቡም ነበር።

7. በቤተ መቅደሱ ዙሪያ ያሉት ክፍሎች ስፋት በየደርቡ እየጨመረ የሚሄድ ነው። በቤተ መቅደሱ ዙሪያ ያለው ሕንጻ አሠራሩ ከታች ወደ ላይ እየሰፋ የሚሄድ በመሆኑ፣ ወደ ላይ በተሄደ ቍጥር የክፍሎቹ ስፋት እየጨመረ የሚሄድ ነው። በመካከለኛው ደርብ በኩል አድርጎ ከታች ወደ ላይ የተዘረጋም ደረጃ አለ።

8. ቤተ መቅደሱ ዙሪያውን ከፍ ብሎ የተሠራ መሠረት ያለው መሆኑን አየሁ፤ ይህ ግራና ቀኝ ላሉት ክፍሎች መሠረት ሲሆን፣ ርዝመቱ ስድስት ክንድ ነው፤ ይህም የዘንጉ ቁመት ነበር።

9. በውጭ በኩል ያለው የግራና የቀኙ ክፍሎች ግንብ ውፍረት አምስት ክንድ ነበር፤ ክፍቱ ቦታ በቤተ መቅደሱና

10. በካህናቱ ክፍሎች መካከል ያለ ሲሆን፣ ስፋቱ በቤተ መቅደሱ ዙሪያ ሃያ ክንድ ነበር።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሕዝቅኤል 41