ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሕዝቅኤል 41:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ከዚያም ወደ መቅደሱ አገባኝ፤ ዐምዶቹንም ለካ፤ የዐምዶቹም ወርድ በአንዱ በኩል ስድስት ክንድ፣ በሌላውም በኩል ስድስት ክንድ ነበር።

2. የመግቢያውም በር ወርድ ዐሥር ክንድ ሲሆን፣ በግራና በቀኝ በኩል ወጣ ወጣ ያሉት ግንቦች ወርድ አምስት ክንድ ነበር። ደግሞም የውስጡን መቅደስ ለካ፤ ርዝመቱ አርባ ክንድ፣ ወርዱም ሃያ ክንድ ነበር።

3. ከዚያም ወደ ውስጥ ገባ፤ የመግቢያውን ዐምዶች ለካ፤ የእያንዳንዱም ወርድ ሁለት ክንድ ነበር። የመግቢያውም ወርድ ስድስት ክንድ ሲሆን፣ ግራና ቀኝ ወጣ ወጣ ያሉት ግንቦች ወርድ ደግሞ ሰባት ክንድ ነበር።

4. እርሱም የውስጠኛውን መቅደስ ርዝመት ለካ፤ ሃያ ክንድ ነበር፤ ወርዱም የውጪውን ግድግዳ ጨምሮ ሃያ ክንድ ነበር፤ እርሱም፣ “ይህ ቅድስተ ቅዱሳን ነው” አለኝ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሕዝቅኤል 41