ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሕዝቅኤል 35:12-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. ከዚያም ስለ እስራኤል ተራሮች፣ “ጠፍ ሆነዋል፤ ቦጫጭቀን እንድንበላቸው ለእኛ ተሰጥተዋል” ብለህ በንቀት የተናገርኸውን እኔ እግዚአብሔር እንደ ሰማሁ በዚያን ጊዜ ታውቃለህ።

13. በእኔ ላይ ታብየሃል፤ በድፍረትም በእኔ ላይ ተናግረሃል፤ እኔም ሰምቼዋለሁ።

14. ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ መላዪቷ ምድር በምትደሰትበት ጊዜ አንተን ባድማ አደርግሃለሁ።

15. የእስራኤል ቤት ርስት ባድማ በሆነች ጊዜ ስለ ተደሰትህ፣ እኔም እንዲሁ አደርግብሃለሁ። የሴይር ተራራ ሆይ፤ አንተና መላዋ ኤዶም ባድማ ትሆናላችሁ፤ ከዚያም እኔ እግዚአብሔር እንደሆንሁ ያውቃሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሕዝቅኤል 35