ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሕዝቅኤል 32:4-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. በምድር ላይ እጥልሃለሁ፤ሜዳም ላይ እዘረጋሃለሁ፤የሰማይ ወፎች ሁሉ እንዲሰፍሩብህ አደርጋለሁ፤የምድር አራዊት ሁሉ በመስገብገብ ይበሉሃል።

5. ሥጋህን በተራሮች ላይ እበታትነዋለሁ፤የተረፈውንም በየሸለቆው እሞላዋለሁ።

6. እስከ ተራሮች ባለው መንገድ ሁሉ፣በሚፈሰው ደምህ ምድሪቱን አርሳታለሁ፤ሸለቆዎችም በሥጋህ ይሞላሉ።

7. አንተን በማጠፋ ጊዜ ሰማያትን እሸፍናለሁ፤ከዋክብታቸውንም አጨልማለሁ፤ፀሓይን በደመና እሸፍናለሁ፤ጨረቃም ብርሃኗን አትሰጥም።

8. በሰማይ የሚያበሩትን ብርሃናት ሁሉ፣በአንተ ላይ አጨልማለሁ፤በምድርህ ላይ ጨለማን አመጣለሁ፤ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

9. በማታውቀው ምድር፣በሕዝቦች መካከል ያንተን ጥፋት ሳመጣ፣የብዙ ሕዝብን ልብ አስጨንቃለሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሕዝቅኤል 32