ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሕዝቅኤል 30:1-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤

2. “የሰው ልጅ ሆይ፤ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በል፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ ‘ዋይ! በል፤ እንዲህም በል፤“ወዮ ለዚያ ቀን!”

3. ቀኑ ቅርብ ነው፤ የእግዚአብሔር ቀን ቅርብ ነው፤የደመና ቀን፣ለአሕዛብም የጥፋት ቀን ነው።

4. በግብፅ ላይ ሰይፍ ይሆናል፤በኢትዮጵያም ላይ ጭንቀት ይመጣል።የታረዱት በግብፅ ሲወድቁ፣ሀብቷ ይወሰዳል፤መሠረቶቿም ይፈርሳሉ።

5. ኢትዮጵያና ፉጥ፣ ልድያና መላው ዐረብ፣ ሊብያና የቃል ኪዳኑ ምድር ሕዝብ ከግብፅ ጋር በአንድነት በሰይፍ ይወድቃሉ።

6. “ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ ‘የግብፅ ተባባሪዎች ይወድቃሉ።የምትኵራራበት ብርታቷ ይወድቃል።ከሚግዶል እስከ አስዋን፣በውስጧ በሰይፍ ይወድቃሉ፤ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

7. “ ‘በባድማ መሬቶች መካከል፣ባድማ ይሆናሉ፤ከተሞቻቸውም፣ከፈራረሱ ከተሞች መካከል ይሆናሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሕዝቅኤል 30