ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሕዝቅኤል 28:6-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. “ ‘ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ ‘እንደ አምላክ ጥበበኛ ነኝ፤ ብለህስለምታስብ፣

7. ከአሕዛብ መካከል እጅግ ጨካኞች የሆኑትን ባዕዳን፣በአንተ ላይ አመጣለሁ፤በጥበብህ ውበት ላይ ሰይፋቸውን ይመዛሉ፤ታላቅ ክብርህንም ያረክሳሉ።

8. ወደ ጒድጓድ ያወርዱሃል፤በጥልቁም ባሕር ውስጥ፣በባሕሮችም ልብ ውስጥ አስከፊ ሞት ትሞታለህ።

9. ታዲያ በገዳዮችህ ፊት፣“አምላክ ነኝ” ትላለህን?በገዳዮችህ እጅ ስትገባ፣አንተ ሰው እንጂ አምላክ አይደለህም።

10. በባዕዳን እጅ፣ያልተገረዙትን ሰዎች አሟሟት ትሞታለህ፤እኔ ተናግሬአለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።’ ”

11. የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤

12. “የሰው ልጅ ሆይ፤ ስለ ጢሮስ ንጉሥ ሙሾ አውርድ፤ እንዲህም በለው፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ ‘ጥበብን የተሞላህ፣ ፍጹም ውበትን የተላበስህ፣የፍጹምነት ምሳሌ ነበርህ።

13. በእግዚአብሔር የአትክልት ቦታ፣በዔድን ነበርህ፤እያንዳንዱ የከበረ ድንጋይ አስጊጦህ ነበር፤ሰርድዮን፣ ቶጳዝዮን፣ አልማዝ፣መረግድ፣ ኢያሰጲድ፣ ሰንፔር፣በሉር፣ ቢረሌና የከበረ ዕንቍ።ልብስህም የሚያብረቀርቅ ዕንቍ ወርቅ ነበር፤የተዘጋጁትም አንተ በተፈጠርህበት ዕለት ነበር።

14. ጠባቂ ኪሩብ ሆነህ ተቀብተህ ነበር፤ለዚሁም ሾምሁህ፤በእግዚአብሔር ቅዱስ ተራራ ላይ ነበርህ፤በእሳት ድንጋዮች መካከል ተመላለስህ።

15. ከተፈጠርህበት ቀን ጀምሮ፣ክፋት እስከ ተገኘብህ ድረስ፣በመንገድህ ነቀፌታ አልነበረብህም።

16. ንግድህ ስለ ደረጀ፣በዐመፅ ተሞላህ፣ኀጢአትም ሠራህ፤ስለዚህ ከእግዚአብሔር ተራራ በውርደት አሳደድሁህ፤ጠባቂ ኪሩብ ሆይ፤ ከእሳት ድንጋዮችመካከል አስወጣሁህ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሕዝቅኤል 28