ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሕዝቅኤል 28:1-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤

2. “የሰው ልጅ ሆይ፤ ለጢሮስ ገዥ እንዲህ በለው፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ ‘ልብህ በትዕቢት ተወጥሮ፣“እኔ አምላክ ነኝ፤በአምላክ ዙፋን ላይ፣በባሕሮችም ልብ ተቀምጫለሁ” አልህ።ምንም እንኳ እንደ አምላክ ጠቢብ ነኝ ብለህ ብታስብም፣አንተ ሰው እንጂ አምላክ አይደለህም።

3. ከዳንኤል ይልቅ ጠቢብ ነህን?ከአንተስ የተሰወረ ምስጢር የለምን?

4. በጥበብህና በማስተዋልህ፣የራስህን ሀብት አከማቸህ፤ወርቅም ብርም፣በግምጃ ቤትህ አጠራቀምህ።

5. በንግድ ሥራ እጅግ ከመራቀቅህ የተነሣ፣በሀብት ላይ ሀብት አካበትህ፤ከሀብትህ ብዛት የተነሣም፤ልብህ በትዕቢት ተወጠረ።

6. “ ‘ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ ‘እንደ አምላክ ጥበበኛ ነኝ፤ ብለህስለምታስብ፣

7. ከአሕዛብ መካከል እጅግ ጨካኞች የሆኑትን ባዕዳን፣በአንተ ላይ አመጣለሁ፤በጥበብህ ውበት ላይ ሰይፋቸውን ይመዛሉ፤ታላቅ ክብርህንም ያረክሳሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሕዝቅኤል 28