ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሕዝቅኤል 28:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤

2. “የሰው ልጅ ሆይ፤ ለጢሮስ ገዥ እንዲህ በለው፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ ‘ልብህ በትዕቢት ተወጥሮ፣“እኔ አምላክ ነኝ፤በአምላክ ዙፋን ላይ፣በባሕሮችም ልብ ተቀምጫለሁ” አልህ።ምንም እንኳ እንደ አምላክ ጠቢብ ነኝ ብለህ ብታስብም፣አንተ ሰው እንጂ አምላክ አይደለህም።

3. ከዳንኤል ይልቅ ጠቢብ ነህን?ከአንተስ የተሰወረ ምስጢር የለምን?

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሕዝቅኤል 28