ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሕዝቅኤል 24:3-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. ለዚህ ዐመፀኛ ቤት እንዲህ ብለህ ተምሳሌት ተናገር፤ ‘ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ ‘ብረት ድስት በእሳት ላይ ጣድ፤ከጣድህም በኋላ ውሃ ጨምርበት።

4. ሙዳ፣ ሙዳ ሥጋ፣ምርጥ ምርጡን ቍርጥ ሁሉ፣ ጭንና ወርቹን ጨምርበት፤የተመረጡ ዐጥንቶችንም ሙላበት።

5. ከመንጋው ሙክቱን ውሰድ፤ዐጥንቱን ለማብሰል ብዙ ማገዶ ከሥሩ ጨምር፤ሙክክ እስከሚል ቀቅለው፤ዐጥንቱም ይብሰል።

6. “ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤“ ‘ለዛገችው ብረት ድስትዝገቷም ለማይለቅ፣ደም ላፈሰሰችው ከተማ ወዮላት!መለያ ዕጣ ሳትጥልአንድ በአንድ አውጥተህ ባዶ አድርገው።

7. “ ‘የሰው ደም በመካከሏ አለ፤በገላጣ ዐለት ላይ አደረገችው እንጂ፣ዐፈር ሊሸፍነው በሚችል፣በመሬት ላይ አላፈሰሰችውም።

8. ቍጣዬ እንዲነድና ለመበቀል እንዲያመቸኝ፣ይሸፈንም ዘንድ እንዳይችል፣ደሟን በገላጣ ዐለት ላይ አፈሰስሁ።

9. “ ‘ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ ‘ደም ላፈሰሰችው ከተማ ወዮላት!እኔም ደግሞ የምትቃጠልበትን ማገዶ እቈልላለሁ።

10. ማገዶውን ከምርበት፤እሳቱን አንድድ፤ቅመም ጨምረህበት፣ሥጋውን በሚገባ ቀቅል፤ዐጥንቱም ይረር።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሕዝቅኤል 24