ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሕዝቅኤል 24:10-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. ማገዶውን ከምርበት፤እሳቱን አንድድ፤ቅመም ጨምረህበት፣ሥጋውን በሚገባ ቀቅል፤ዐጥንቱም ይረር።

11. ጒድፉ እንዲቀልጥ፣ዝገቱም በእሳት እንዲበላ፣ባዶው ድስት እስኪሞቅ፣መደቡም እስኪግል ከሰል ላይ ጣደው።

12. ብዙ ጒልበት ቢፈስበትም፣የዝገቱ ክምር፣በእሳት እንኳ፣ ሊለቅ አልቻለም።

13. “ ‘የረከስሽው በብልግናሽ ነው፤ ቍጣዬ በአንቺ ላይ እስኪፈጸም ድረስ ከእንግዲህ ንጹሕ አትሆኚም፤ ከርኵሰትሽ ላነጻሽ ፈልጌ፣ መንጻት አልወደድሽምና።

14. “ ‘እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ፤ የምሠራበትም ጊዜ ደርሶአል፤ ወደ ኋላ አልልም፤ አልራራም፤ አላመነታምም። እንደ መንገድሽና እንደ ተግባርሽ ይፈረድብሻል፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።’ ”

15. የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤

16. “የሰው ልጅ ሆይ፤ የዐይንህ ማረፊያ የሆነውን ነገር በመቅሠፍት እወስድብሃለሁ፤ አንተ ግን ዋይታ አታሰማ፤ አታልቅስ፤ እንባህንም አታፍስስ፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሕዝቅኤል 24