ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሕዝቅኤል 24:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. በዘጠነኛው ዓመት፣ በዐሥረኛው ወር፣ በዐሥረኛው ቀን የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤

2. “የሰው ልጅ ሆይ፤ ይህን ቀን፣ የዛሬውን ዕለት ለይተህ መዝግብ፤ የባቢሎን ንጉሥ ኢየሩሳሌምን በዚህ ቀን ከቦአታልና።

3. ለዚህ ዐመፀኛ ቤት እንዲህ ብለህ ተምሳሌት ተናገር፤ ‘ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ ‘ብረት ድስት በእሳት ላይ ጣድ፤ከጣድህም በኋላ ውሃ ጨምርበት።

4. ሙዳ፣ ሙዳ ሥጋ፣ምርጥ ምርጡን ቍርጥ ሁሉ፣ ጭንና ወርቹን ጨምርበት፤የተመረጡ ዐጥንቶችንም ሙላበት።

5. ከመንጋው ሙክቱን ውሰድ፤ዐጥንቱን ለማብሰል ብዙ ማገዶ ከሥሩ ጨምር፤ሙክክ እስከሚል ቀቅለው፤ዐጥንቱም ይብሰል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሕዝቅኤል 24