ምዕራፎች

  1. 1
  2. 2
  3. 3
  4. 4
  5. 5
  6. 6
  7. 7
  8. 8
  9. 9
  10. 10
  11. 11
  12. 12
  13. 13
  14. 14
  15. 15
  16. 16
  17. 17
  18. 18
  19. 19
  20. 20
  21. 21
  22. 22
  23. 23
  24. 24
  25. 25
  26. 26
  27. 27
  28. 28
  29. 29
  30. 30
  31. 31
  32. 32
  33. 33
  34. 34
  35. 35
  36. 36
  37. 37
  38. 38
  39. 39
  40. 40
  41. 41
  42. 42
  43. 43
  44. 44
  45. 45
  46. 46
  47. 47
  48. 48

ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሕዝቅኤል 19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ስለ እስራኤል መሳፍንት የወጣ ሙሾ

1. “ስለ እስራኤል መሳፍንት ሙሾ አውጣ፤

2. እንዲህም በል፤“ ‘እናትህ በአንበሶች መካከል እንዴትያለች አንበሳ ነበረች!በደቦል አንበሶች መካከል ተጋደመች፤ግልገሎቿንም በዚያ አሳደገች።

3. ከግልገሎቿ መካከል አንዱን አሳደገችው፤እርሱም ብርቱ አንበሳ ሆነ።ግዳይ መንጠቅን ተማረ፤ሰዎችንም በላ።

4. አሕዛብም ስለ እርሱ ሰሙ፤በጒድጓዳቸውም ገብቶ ተያዘ፤እነርሱም በስናግ ጐትተው፣ወደ ግብፅ ምድር ወሰዱት።

5. “ ‘ተስፋዋ መጨናገፉን፣የጠበቀችውም አለመሳካቱን ባየች ጊዜ፣ከግልገሎቿ ሌላውን ወስዳ፣ብርቱ አንበሳ አድርጋ አሳደገችው።

6. እርሱም በአንበሶች መካከል ተጐማለለ፤እየበረታም ሄደ፤ግዳይ መንጠቅን ተማረሰዎችንም በላ።

7. ምሽጎቻቸውን አወደመ፤ከተሞቻቸውንም ባድማ አደረገ፤ምድሪቷና በውስጧ ያሉት ሁሉ፣ከግሣቱ የተነሣ ተንቀጠቀጡ።

8. በዙሪያው ያሉ አሕዛብ ተነሡበት፤ከየአገሩም ሁሉ ተሰበሰቡበት፤መረባቸውን ዘረጉበት፤በጒድጓዳቸውም ገብቶ ተያዘ።

9. በስናግም በመጐተት ቀፎ ውስጥ ከተው፣ወደ ባቢሎን ንጉሥ አመጡት፤ድምፁ በእስራኤል ተራሮች ላይ፣ዳግመኛ እንዳይሰማ፣በእስር ቤት አኖሩት።

10. “ ‘እናትህ በውሃ አጠገብ የተተከለ፣በዕርሻ ውስጥ ያለ፣ከውሃም ብዛት የተነሣ፣ያፈራና የተንሰራፋ የወይን ተክልመሰለች።

11. ቅርንጫፎቿ ለበትረ መንግሥትየሚሆኑ፣ ጠንካሮች ነበሩ፤ጥቅጥቅ ባሉ ቅጠሎች መካከል፣በቁመቷና በብዙ ቅርንጫፎቿ፣ዘለግ ብላ፣ ጐልታ ትታይ ነበር።

12. ነገር ግን በቍጣ ተነቀለች፤ወደ ምድርም ተጣለች።የምሥራቅ ነፋስ አደረቃት፤ፍሬዎቿንም አረገፈባት።ብርቱዎቹ ቅርንጫፎቿ ክው አሉ፤እሳትም በላቸው።

13. አሁን ውሃ በተጠማ ደረቅ ምድር፣በበረሓ ውስጥ ተተከለች።

14. ከዋና ቅርንጫፎቿ ከአንዱ እሳት ወጣ፤ፍሬዋንም በላ።በትረ መንግሥት የሚሆን፣አንድም ጠንካራ ቅርንጫፍ አልተረፈም።’ይህ ሙሾ ነው፤ ለሐዘን እንጒርጒሮም ይሆናል።’