ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሕዝቅኤል 18:9-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. ሥርዐቴን ይከተላል፤ሕጌንም በቅንነት ይጠብቃል።ይህ ሰው ጻድቅ ነው፤ፈጽሞ በሕይወት ይኖራል፤ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

10. “ነገር ግን ይህ ሰው ደም የሚያፈስ ወይም ከሚከተሉት ኀጢአቶች ማንኛውንም የሚፈጽም ዐመፀኛ ልጅ ቢኖረው፣

11. አባትየው አንዱንም ባያደርግ፣“ልጁ ግን በኰረብታ መስገጃ የቀረበውን ቢበላ፣የባልንጀራውን ሚስት ቢያባልግ፣

12. ድኻውንና ችግረኛውን ቢጨቍን፣በጒልበት ቢቀማ፣በመያዣነት የወሰደውን ባይመልስ፣ወደ ጣዖታት ቢመለከት፣አስጸያፊ ተግባራትን ቢፈጽም፣

13. በዐራጣ ቢያበድር፤ ከፍተኛ ወለድም ቢቀበል፣እንዲህ ዐይነቱ ሰው በሕይወት ይኖራልን? ከቶ አይኖርም! እነዚህን አስጸያፊ ነገሮች አድርጓልና በእርግጥ ይሞታል፤ ደሙም በገዛ ራሱ ላይ ይሆናል።

14. “ይህም ልጅ ደግሞ በተራው ልጅ ቢወልድና ልጁም አባቱ ያደረገውን ኀጢአት ሁሉ አይቶ ባይፈጽም፣ ይኸውም፦

15. በኰረብታ መስገጃ የቀረበውን ባይበላ፣በእስራኤል ቤት ወዳሉት ጣዖታት ባይመለከት፣የባልንጀራውን ሚስት ባያባልግ፣

16. ሰውን ባይጨቍን፣ብድር ለመስጠት መያዣ ባይጠይቅ፣በጒልበቱ ባይቀማ፣ነገር ግን ምግቡን ለተራበ፣ልብሱን ለተራቈተ ቢሰጥ፣

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሕዝቅኤል 18