ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሕዝቅኤል 18:1-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤

2. “ስለ እስራኤል ምድር፣“ ‘አባቶች ጐምዛዛ የወይን ፍሬ በሉ፤የልጆችንም ጥርስ አጠረሰ’ እያላችሁ የምትመስሉት ተምሳሌት ምን ለማለት ነው?

3. “በሕያውነቴ እምላለሁ ይላል ልዑል እግዚአብሔር፤ ከእንግዲህ ይህን ምሳሌ በእስራኤል ምድር አትመስሉም።

4. እነሆ ነፍስ ሁሉ የእኔ ናት፤ የአባት ነፍስ የእኔ እንደሆነች ሁሉ የልጁም ነፍስ የእኔ ናት፤ ኀጢአት የምትሠራ ነፍስ እርሷ ትሞታለች።

5. “በቅንነትና በትክክል የሚሠራ፣ጻድቅ ሰው ቢገኝ፣

6. በኰረብታ ባሉ አብያተ ጣዖት የቀረበውን አይበላም፤በእስራኤል ቤት ወዳሉት ጣዖታት አይመለከትምየባልንጀራውን ሚስት አያባልግም፤ከሴት ጋር በወር አበባዋ ጊዜ አይተኛም።

7. ማንንም አይጨቍንም፤ነገር ግን በመያዣ የወሰደውን እንኳ ለተበዳሪው ይመልሳል፤ለተራበ የራሱን እንጀራ፣ለተራቈተም ልብስ ይሰጣል እንጂ፣በጒልበት አይቀማም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሕዝቅኤል 18