ምዕራፎች

  1. 1
  2. 2
  3. 3
  4. 4
  5. 5
  6. 6
  7. 7
  8. 8
  9. 9
  10. 10
  11. 11
  12. 12
  13. 13
  14. 14

ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሆሴዕ 9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

በእስራኤል ላይ የሚደርሰው ቅጣት

1. እስራኤል ሆይ፤ ደስ አይበልሽ፤እንደ ሌሎችም ሕዝቦች ሐሤት አታድርጊ፤ለአምላክሽ ታማኝ አልሆንሽምና፤በየእህል ዐውድማውም ላይ፣ለጋለሞታ የሚከፈለውን ዋጋ ወደሻል።

2. የእህል አውድማዎችና የወይን መጭመቂያዎች ሕዝቡን አይመግቡም፤አዲሱም የወይን ጠጅ ይጐድልባቸዋል።

3. በእግዚአብሔር ምድር አይቀመጡም፤ኤፍሬም ወደ ግብፅ ይመለሳል፤የረከሰውንም ምግብ በአሦር ይበላል።

4. የወይን ጠጅን ቍርባን ለእግዚአብሔር አያፈሱም፤መሥዋዕታቸውም ደስ አያሰኘውም፤እንዲህ ዐይነቱ መሥዋዕት ለእነርሱ የሐዘንተኞች እንጀራ ይሆንባቸዋል፤የሚበሉትም ሁሉ ይረክሳሉ።ይህ ምግብ ለገዛ ራሳቸው ይሆናል፤ወደ እግዚአብሔርም ቤተ መቅደስ አይገባም።

5. በእግዚአብሔር የበዓል ቀናት፣በዓመት በዓሎቻችሁም ቀን ምን ታደርጋላችሁ?

6. ከጥፋት ቢያመልጡም እንኳ፣ግብፅ ትሰበስባቸዋለች፤ሜምፎስም ትቀብራቸዋለች።የብር ሀብታቸውን ዳዋ ያለብሰዋል፤ድንኳኖቻቸውም እሾኽ ይወርሰዋል።

7. የቅጣት ቀን መጥቶአል፤የፍርድም ቀን ቀርቦአል፤እስራኤልም ይህን ይወቅ!ኀጢአታችሁ ብዙ፣ጠላትነታችሁም ታላቅ ስለ ሆነ፣ነቢዩ እንደ ሞኝ፣መንፈሳዊውም ሰው እንደ እብድ ተቈጥሮአል።

8. ነቢዩ ከአምላኬ ጋር ሆኖ፣የኤፍሬም ጠባቂ ነው፤ዳሩ ግን በመንገዱ ሁሉ ወጥመድ፣በአምላኩም ቤት ጠላትነት ይጠብቀዋል።

9. በጊብዓ እንደ ነበረው፣በርኵሰት ውስጥ ተዘፍቀዋል፤እግዚአብሔር ክፋታቸውን ያስባል፤ስለ ኀጢአታቸውም ይቀጣቸዋል።

10. “እስራኤልን ማግኘቴ፣የወይንን ፍሬ፣ በምድረ በዳ የማግኘት ያህል ነበር፤አባቶቻችሁንም ማየቴ፣የመጀመሪያውን የበለስ ፍሬ የማየት ያህል ነበር፤ወደ ብዔልፌጎር በመጡ ጊዜ ግን፣ለዚያ አሳፋሪ ጣዖት ራሳቸውን ለዩ፤እንደ ወደዱትም ጣዖት የረከሱ ሆኑ።

11. የኤፍሬም ክብር እንደ ወፍ በሮ ይጠፋል፤መውለድ፣ ማርገዝና መፀነስ የለም።

12. ልጆችን ቢያሳድጉ እንኳ፣ልጅ አልባ እስኪሆኑ ድረስ እነጥቃቸዋለሁ፤ፊቴን ከእነርሱ በመለስሁ ጊዜ፣ወዮ ለእነርሱ

13. ኤፍሬምን እንደ ጢሮስ፣በመልካም ስፍራ ተተክሎ አየሁት፤አሁን ግን ኤፍሬም ልጆቹን፣ለነፍሰ ገዳዮች አሳልፎ ይሰጣል።”

14. እግዚአብሔር ሆይ፤ ስጣቸው፤ምን ትሰጣቸዋለህ?የሚጨነግፉ ማሕፀኖችን፣የደረቁ ጡቶችን ስጣቸው።

15. “በጌልገላ ካደረጉት ክፋታቸው ሁሉ የተነሣ፣እኔ በዚያ ጠላኋቸው፤ስለሠሩት ኀጢአት፣ከቤቴ አሳድዳቸዋለሁ፤ከእንግዲህም አልወዳቸውም፤መሪዎቻቸው ሁሉ ዐመፀኞች ናቸው።

16. ኤፍሬም ተመታ፤ሥራቸው ደረቀ፤ፍሬም አያፈሩም፤ልጆች ቢወልዱም እንኳ፣ተንከባክበው ያሳደጓቸውን ልጆቻቸውን እገድላለሁ።”