ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሆሴዕ 14:4-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. “እኔ ከዳተኛነታቸውን እፈውሳለሁ፤እንዲሁ እወዳቸዋለሁ፤ቊጣዬ ከእነርሱ ተመልሶአልና።

5. እኔ ለእስራኤል እንደ ጠል እሆናለሁ፤እንደ ውብ አበባ ያብባል፤እንደ ሊባኖስ ዝግባም፣ሥር ይሰዳል፤

6. ቅርንጫፉ ያድጋል፤ውበቱ እንደ ወይራ ዛፍ፣ሽታውም እንደ ሊባኖስ ዝግባ ይሆናል።

7. ሰዎች እንደ ገና ከጥላው በታች ያርፋሉ፤እርሱም እንደ እህል ይለመልማል፤እንደ ወይን ተክል ያብባል፤ዝናውም እንደ ሊባኖስ የወይን ጠጅ ይወጣል።

8. ኤፍሬም ሆይ፤ ከእንግዲህ ከጣዖት ጋርምን ጒዳይ አለኝ?የምሰማህና የምጠነቀቅልህ እኔ ነኝ፤እኔ እንደለመለመ የጥድ ዛፍ ነኝ፤ፍሬያማነትህም ከእኔ የተነሣ ነው።”

9. ጥበበኛ የሆነ እነዚህን ነገሮች ያስተውላል፤አስተዋይም እነዚህን ነገሮች ይረዳል። የእግዚአብሔር መንገድ ቅን ነውና፤ጻድቃን ይሄዱበታል፤ዐመፀኞች ግን ይሰናከሉበታል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሆሴዕ 14