ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሆሴዕ 14:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እስራኤል ሆይ፤ በኀጢአትህ ምክንያት ስለ ወደቅህ፣ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ተመለስ።

2. የምትሉትን ቃል ይዛችሁ፣ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ፤እንዲህም በሉት፤“ኀጢአታችንን ሁሉ ይቅር በለን፤የከንፈራችንንም ፍሬ እንድናቀርብ፣በምሕረትህ ተቀበለን።

3. አሦር ሊያድነን አይችልም፤በጦር ፈረሶችም ላይ አንቀመጥም፤ከእንግዲህም የገዛ እጆቻችን የሠሯቸውን፣‘አምላኮቻችን’ አንላቸውም፤ድኻ አደጉ ከአንተ ርኅራኄ ያገኛልና።”

4. “እኔ ከዳተኛነታቸውን እፈውሳለሁ፤እንዲሁ እወዳቸዋለሁ፤ቊጣዬ ከእነርሱ ተመልሶአልና።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሆሴዕ 14