ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሆሴዕ 10:7-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. ሰማርያና ንጉሥዋ፣በውሃ ላይ እንዳለ ኩበት ተንሳፍፈው ይጠፋሉ።

8. የእስራኤል ኀጢአት የሆነው፣የአዌን ማምለኪያ ኰረብታ ይጠፋል፤እሾኽና አሜኬላ ይበቅልባቸዋል፤መሠዊያዎቻቸውንም ይወርሳል፤በዚያን ጊዜ ተራሮችን፣ “ሸፍኑን!”ኰረብታዎችንም፣ “ውደቁብን!” ይላሉ።

9. “እስራኤል ሆይ፤ ከጊብዓ ጊዜ ጀምሮ ኀጢአት ሠራችሁ፤በዚያም ጸናችሁ፤በጊብዓ የነበሩትን ክፉ አድራጊዎች፣ጦርነት አልጨረሳቸውምን?

10. በፈለግሁ ጊዜ እቀጣቸዋለሁ፤ስለ ድርብ ኀጢአታችሁም ይቀጧቸው ዘንድ፣በእነርሱ ላይ ይሰበሰባሉ፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሆሴዕ 10