ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሆሴዕ 10:5-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. በሰማርያ የሚኖረው ሕዝብ፣በቤትአዌን ስላለው የጥጃ ጣዖት ይፈራል፤ሕዝቡም ያለቅስለታል፤በክብሩ እጅግ ደስ ያላቸው ሁሉ፣አመንዝራ ካህናትም እንደዚሁ ያለቅሱለታል፤በምርኮ ከእነርሱ ተወስዶአልና።

6. ለታላቁ ንጉሥ እንደ እጅ መንሻ፣ወደ አሦር ይወሰዳል፤ኤፍሬም ይዋረዳል፤እስራኤልም ስለ ጣዖቱ ያፍራል።

7. ሰማርያና ንጉሥዋ፣በውሃ ላይ እንዳለ ኩበት ተንሳፍፈው ይጠፋሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሆሴዕ 10