ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሆሴዕ 10:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እስራኤል የተንዠረገገ ወይን ነበር፤ብዙ ፍሬም አፈራ፤ፍሬው በበዛ መጠን፣ብዙ መሠዊያዎችን ሠራ፤ምድሩ በበለጸገ መጠን፣የጣዖታት ማምለኪያ ዐምዶችን አስጌጠ።

2. ልባቸው አታላይ ነው፤ስለዚህም በደላቸውን ይሸከማሉ። እግዚአብሔር መሠዊያዎቻቸውን ያወድማል፤የጣዖት ማምለኪያ ዐምዶቻቸውን ያፈራርሳል።

3. እነርሱም፣ “እኛ ንጉሥ የለንም፤ እግዚአብሔርን አላከበርንምና፤ንጉሥ ቢኖረንስ፣ምን ሊያደርግልን ይችል ነበር?” ይላሉ።

4. ከንቱ ተስፋ ይሰጣሉ፤በሐሰት በመማል፣ቃል ኪዳን ያደርጋሉ፤ስለዚህም ፍርድ፣በዕርሻ ውስጥ እንደሚገኝ መርዛማ ዐረም ይበቅላል።

5. በሰማርያ የሚኖረው ሕዝብ፣በቤትአዌን ስላለው የጥጃ ጣዖት ይፈራል፤ሕዝቡም ያለቅስለታል፤በክብሩ እጅግ ደስ ያላቸው ሁሉ፣አመንዝራ ካህናትም እንደዚሁ ያለቅሱለታል፤በምርኮ ከእነርሱ ተወስዶአልና።

6. ለታላቁ ንጉሥ እንደ እጅ መንሻ፣ወደ አሦር ይወሰዳል፤ኤፍሬም ይዋረዳል፤እስራኤልም ስለ ጣዖቱ ያፍራል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሆሴዕ 10