ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሆሴዕ 10:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እስራኤል የተንዠረገገ ወይን ነበር፤ብዙ ፍሬም አፈራ፤ፍሬው በበዛ መጠን፣ብዙ መሠዊያዎችን ሠራ፤ምድሩ በበለጸገ መጠን፣የጣዖታት ማምለኪያ ዐምዶችን አስጌጠ።

2. ልባቸው አታላይ ነው፤ስለዚህም በደላቸውን ይሸከማሉ። እግዚአብሔር መሠዊያዎቻቸውን ያወድማል፤የጣዖት ማምለኪያ ዐምዶቻቸውን ያፈራርሳል።

3. እነርሱም፣ “እኛ ንጉሥ የለንም፤ እግዚአብሔርን አላከበርንምና፤ንጉሥ ቢኖረንስ፣ምን ሊያደርግልን ይችል ነበር?” ይላሉ።

4. ከንቱ ተስፋ ይሰጣሉ፤በሐሰት በመማል፣ቃል ኪዳን ያደርጋሉ፤ስለዚህም ፍርድ፣በዕርሻ ውስጥ እንደሚገኝ መርዛማ ዐረም ይበቅላል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሆሴዕ 10