ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

2 ዜና መዋዕል 4:8-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. ዐሥር ጠረጴዛ ሠርቶም ወደ ቤተ መቅደሱ በማስገባት አምስቱን በስተ ደቡብ፣ አምስቱን ደግሞ በስተ ሰሜን በኩል አኖራቸው፤ ደግሞም አንድ መቶ ጐድጓዳ የወርቅ ሳሕኖች ሠራ።

9. የካህናቱንም አደባባይ ሠራ፣ እንዲሁም ታላቁን አደባባይና በሮቹን ከሠራ በኋላ በናስ ለበጣቸው።

10. በርሜሉንም ከቤተ መቅደሱ በስተ ደቡብ ምሥራቅ ባለው ማዕዘን በቀኝ በኩል አኖረው።

11. እንዲሁም ምንቸቱን፣ መጫሪያዎችንና ጐድጓዳ ሳሕኖችን ሠራ። ኪራምም ለቤተ መቅደሱ አገልግሎት የሚውሉትን ዕቃዎች ለንጉሥ ሰሎሞን ሠርቶ ጨረሰ፤ እነዚህም

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 2 ዜና መዋዕል 4