ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

2 ዜና መዋዕል 26:19-23 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

19. ጥና በእጁ ይዞ ዕጣን ለማጠን ዝግጁ የነበረው ዖዝያን ተቈጣ፤ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ በዕጣን መሠዊያው ፊት ሆኖ ካህናቱ ላይ እየተቈጣ ሳለ፣ በግንባሩ ላይ ለምጽ ወጣበት።

20. ሊቀ ካህናቱ ዓዛርያስና ሌሎቹ ካህናት ሁሉ በተመለከቱት ጊዜ፣ በግንባሩ ላይ ለምጽ እንደ ወጣበት አዩ። ስለዚህ አጣድፈው አስወጡት፤ በእርግጥ እርሱም ራሱ ለመውጣት ቸኵሎ ነበር፤ እግዚአብሔር አስጨንቆታልና።

21. ንጉሥ ዖዝያን እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ ለምጻም ነበረ። ለምጻም በመሆኑም ከቤተ መቅደስ ተወግዶ ነበርና በተለየ ቤት ተቀመጠ። ከዚያም ልጁ ኢዮአታም የቤተ መንግሥቱን አስተዳደር በኀላፊነት ተረክቦ የአገሩን ሕዝብ ይመራ ጀመር።

22. በዖዝያን ዘመነ መንግሥት ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው የተከናወነውን ሌላውን ተግባር ሁሉ የአሞጽ ልጅ ነቢዩ ኢሳይያስ ጽፎታል።

23. ዖዝያንም እንደ አባቶቹ ሁሉ አንቀላፋ። ሕዝቡም “ለምጽ አለበት” ብለው የነገሥታቱ በሆነው መቃብር አጠገብ ባለው ቦታ ቀበሩት፤ ልጁም ኢዮአታም በእርሱ ፈንታ ነገሠ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 2 ዜና መዋዕል 26