ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

2 ዜና መዋዕል 24:15-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. ዮዳሄ ሸምግሎ ዕድሜ ከጠገበ በኋላ በመቶ ሠላሳ ዓመቱ ሞተ።

16. እርሱም በእስራኤል ውስጥ ለእግዚአብሔርና ለቤተ መቅደሱ መልካም ሠርቶአልና በዳዊት ከተማ በነገሥታቱ መቃብር ተቀበረ።

17. ከዮዳሄ ሞት በኋላ የይሁዳ ሹማምት መጥተው ለንጉሡ ታማኝነታቸውን ገለጡ፤ ንጉሡም አዳመጣቸው።

18. እነርሱም የአባቶቻቸውን አምላክ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ትተው፣ የአሼራን ዐምዶችና ጣዖታትን አመለኩ፤ በበደላቸውም ምክንያት የእግዚአብሔር ቊጣ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ መጣ።

19. ወደ እግዚአብሔር ይመልሷቸው ዘንድ እርሱ ነቢያቱን ወደ ሕዝቡ ሰደደ፤ ነቢያቱም መሰከሩባቸው፤ እነርሱ ግን አላዳመጡም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 2 ዜና መዋዕል 24