ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

2 ዜና መዋዕል 23:15-21 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. እርሷም በቤተ መንግሥቱ ግቢ የፈረስ መግቢያ በር ወደተባለው ቦታ እንደ ደረሰች ያዟት፤ በዚያም ገደሏት።

16. ዮዳሄም ራሱ፣ ሕዝቡና ንጉሡ የእግዚአብሔር ሕዝብ እንደሚሆኑ ቃል ኪዳን ገባ።

17. ከዚህ በኋላ ሕዝቡ በሙሉ ሄዶ የበኣልን ቤተ ጣዖት አፈረሰው፤ መሠዊያዎቹንና ጣዖታቱን አደቀቀ፤ የበኣልን ካህን ማታንንም በመሠዊያዎቹ ፊት ለፊት ገደሉት።

18. ዮዳሄ በሙሴ ሕግ እንደተጻፈውና ዳዊትም እንዳዘዘው፣ በደስታና በመዝሙር የሚቃጠለውን የእግዚአብሔርን መሥዋዕት እንዲያቀርቡ ዳዊት ለመደባቸው ካህናትና ሌዋውያን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ኀላፊነት ሰጣቸው።

19. እንዲሁም በማንኛውም ነገር የረከሰ ሰው እንዳይገባ፣ በቤተ መቅደሱ ቅጥር በሮች ላይ ጠባቆች አቆመ።

20. የመቶ አለቆቹን፣ መኳንንቱን፣ የሕዝቡን ገዦችና የአገሩን ሕዝብ ሁሉ ይዞ ንጉሡን ከላይ ከቤተ መቅደሱ ወደ ታች አመጣው። በላይኛውም መግቢያ በኩል ወደ ቤተ መንግሥቱ ገብተው ንጉሡን በመንግሥቱ ዙፋን ላይ አስቀመጡት።

21. መላውም የአገሩ ሕዝብ ተደሰተ፤ ጎቶልያ ስለ ተገደለችም ከተማዪቱ ሰላም አግኝታ ነበር።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 2 ዜና መዋዕል 23