ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

2 ዜና መዋዕል 2:15-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. “አሁንም ጌታዬ በሰጠው ተስፋ መሠረት ስንዴውንና ገብሱን፣ የወይራ ዘይቱንና የወይን ጠጁን ለአገልጋዮቹ ይላክ፤

16. እኛም የሚያስፈልግህን ግንድ ሁሉ ከሊባኖስ ቈርጠንና አስረን እስከ ኢዮጴ ድረስ ቍልቍል በማንሳፈፍ እንሰድልሃለን፤ አንተም ወደ ኢየሩሳሌም ታስወስደዋለህ።”

17. ሰሎሞን አባቱ ዳዊት ካደረገው ቈጠራ በኋላ፣ በእስራኤል ምድር የነበሩትን መጻተኞች ሁሉ ቈጠረ፤ ቊጥራቸውም አንድ መቶ አምሳ ሦስት ሺህ ስድስት መቶ ሆነ።

18. ከእነዚህም ሰባ ሺውን ተሸካሚዎች፣ ሰማንያ ሺውን በኰረብታው ላይ ድንጋይ ፈላጮች፣ ሦስት ሺህ ስድስት መቶውን ደግሞ የሥራው ተቈጣጣሪዎች ሆነው ሰዎቹን እንዲያሠሩ መደበ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 2 ዜና መዋዕል 2